የሰብኣዊ መብት አያያዝና ሌሎች አስተዳደራዊና የባለቤትነት መብቶች ላይ ያሉትን ችግሮች በማንሳት አስቾካይ መልስ መጠየቅን ይመለከታል፡፡

ቀን  16 /04/ 2004  ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር

ለክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት

ፊንፊኔ

                                                                                               ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች

                                                                                                      ፊንፊኔ

 

ጉዳዩ:   የሰብኣዊ መብት አያያዝና ሌሎች አስተዳደራዊና የባለቤትነት መብቶች ላይ ያሉትን ችግሮች

      በማንሳት አስቾካይ መልስ መጠየቅን ይመለከታል፡፡

እኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኦሮሞ ተማሪዎች በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ህዝብ ያለበትና ለወደ ፊት ሁኔታውም አስፈሪ የሆኑ ዘርፈ-ብዙና ውስበስብ ችግሮችን ከግንዛቤ በማስገባት ከዚህ በታች ለዘረዘርናቸው የመብትና የባለቤትናት ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ እንድሰጠን እንጠይቃለን፡፡ እነዚህ የምናነሳቸው ጥያቄዎች የኦሮሞ ህዝብ በሀገሩ ሊኖራቸው የሚገቡ ተፈጥሮኣዊ  የባለቤትነት መብቶችና አስተዳደራዊ መብቶች ስለሆኑ ጥያቄዎቹና ለጥያቄዎቹም የሚሰጥ መልስ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ መሆኑን እያስገነዘብን እነዚህን ለህዝባችን እንደ አንድ ህዝብ መኖር ወይም ላለመኖር ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎችን ስንጠይቅ አዎንታዊና ፍትሓዊ መልስ በመስጠጥ ታሪካዊ ግዴታን ይወጣሉ የሚል ተስፋ በማድረግ ነው፡፡

I. የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ሊያገኘው የሚገቡ መብቶች/ልዩ ጥቅም/ እና ባለቤትነት በተመለከተ፡ 

1. ‹‹አዲስ አበባ›› የሚለው ስያሜ የኦሮሞን መሬት ባለቤትነትና ማንነት ለመደበቅ ታስቦ በወራሪው የሚኒልክ ገዢ መደብ የተሰየመ በመሆኑና ህዝባችን የባለቤትነት ስሜት እንዳይሰመው  ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ጫና ስላለው ስያሜው ወደ መጀመሪያው ማለትም የኦሮሞ ህዝብ ቦታው/መሬቱ ካለው ተፈጠሮኣዊ ውበትና እሴት በመነሳት በቋንቋው ‹‹ፊንፊኔ›› ብለው በሰየመው ስም በሀገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ እንድትጠራ  አበክረን እንጠይቃለን፡፡

2. አፋን ኦሮሞ አሁን ባለው የፊንፊኔ አስተዳደር ውስጥ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ጎን ለጎን የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይቺ መሬት የኦሮሞ ህዝብ የተፈጥሮ ሀብት ናት፡፡ በህዝባችን ላይ ከተጫነው የባሪነት ስርኣት የተነሳ በተለያዩ ተፅኖዎች ህዝቡ ተገፍትሮ አሁን በከተማዋ ያለው ቁጥር አናሳ ብሆንም አሁንም ቢሆን ከአማራ ህዝብ ቀጥሎ በከተማዋ የህዝብ ብዛት ንፅፅር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም አሁን በከተማዋ ያለውን አብላጫ ቁጥር በማየት ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ላይ ያለውን ተፈጥሮኣዊ መብቶች ከግንዘቤ በማስገባት አፋን ኦሮሞ(የኦሮሚኛ ቋንቋ) የከተማዋ የሥራ ቋንቋ  እንድሆን ስንጠይቅ አስቾካይ መልስ በመሻት ነው፡፡

3. በህዝብ ምርጫ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ በፊንፊኔ ላይ ባለው ተፈጥሮኣዊ የባለቤትነት መብት በፊንፊኔ ምክር ቤት መቀመጫ እንድኖራው እንጠይቃለን፡፡

4. የአንድን ህዝብ ባህልና ታሪክ ለአለም ለማሰወቅም ሆነ ለማወቅ ቤተ-መፅሓፍትና ሙዚየም የመረጃና ቅርጻ-ቅርጽ/እሴቶች ምንጭ በመሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ በተላይ እንደ ፊንፊኔ ባሉት የብዙ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች መቀመጫ በሆኑ ታላላቅ ከተሞች ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ እስካ አሁን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ አይደለም! ለምን???

5. የኦሮሞ ህዝብ ለሰው ልጅ መልካም ሥራ ሠርተው ያለፉ ምሁራንና ለህዝቡ ነፃነት ስፋለሙ የወደቁ ብዙ  ጀግኖች አለው፡፡ ለነዚህ ምሁራንና ጀግኖች በፊንፊኔ አንዳችም ሃውልት አልቆመላቸውም፤  አንድም መንገድም በስማቸው አልተሰየመም፡፡ ለምን?

6. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ ባሕልና ታሪክ የሚያንጸባርቅ የራሱ የሆነ ቤተ መንግስት የለውም፡፡ ኣብዛኛው ቢሮዎችም ከፊንፊኔ አስተዳዳርና ከግለሰቦች የተከራያቸው ናቸው፡፡ ይህ ለምን ሆነ?

7. ከፊንፊኔ በየአመቱ ከተለያዩ ዘርፎች ከግብር እና ታክሲ እንድሁም ከሌሎች ገቢዎች የሚሰበሰበው በቢሊየን የሚቆጠር ብር ነው፡፡ ይህ ገቢ የፌዴራል መንግስትን ካዝና በማደለብ ለፖለቲካ  ፍጆታ ከመዋል ውጪ ለኦሮሚያና ለኦሮሞ ህዝብ ልማት አንዳችም አስተዋጽኦ አያበረከተ አይደለም፡፡ ይበልጥኑ የፌዴራል መንግስት  በከተማዋ ዙሪያ ያሉትን አርሶ አደሮች በእንቬስትመንት ስም ከይዞታቸው በማፈናቀል መሬቱን ለውጪ ባለሀብቶች እየቸበቸበ ተጨማሪ ገቢን ከኦሮሚያ ያግበሰብሳል፡፡

በመሆኑም ከከተማዋና አከባቢዋ ከሚሰበሰበወ  ገቢ የተወሰነው ወደ ኦሮሚያ በጀት ተዛውሮ ይህም በከተማዋ ለኦሮሞ ህዝብ ልሰሩ የሚገባቸውን የልማት ሥራዎች፡ ለምሳሌ የአፋን ኦሮሞ ት/ቤቶችና የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ሥነ-ጥበብ ማዕከላት እንድሰሩበት እንጠይቃለን፡፡ Iyyannoo barattootaa Oromoo University Finfinnee

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s